መሰረታዊ መረጃዎች
የድርጅቱ ራዕይ
ቤተክርስቲያናችን ከመንፈሳዊና ሀገራዊ አገልግሎቷ ጎንለጎን በቤቶችና ሕንጻዎች አሰተዳደርና ልማት ላይ የምታደርገው እንቅስቃሴ ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ቀላል ፣ፈጣንና ተአማኒ የሆነ አስተዳደር ሥርዓት ተፈጥሮ በቤት ልማቱ ዘርፍም ዘመኑ የሚጠይቀውን ስርዓት ተዘርግቶ ፣በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ተዋዳዳሪና ተመራጭ እንዲሁም ለነሪዎች ምቹ፣ጽዱና ውብ ሕንጻዎች ተገንብተው ማየት ነው፡፡
የድርጅቱ ተልዕኮ
ቤተክርስቲያኒቱ የተሠማራችበትን የቤት ልማት ዘርፍ በሀገራችን የሚታየውን የቤት ችግር ለመቅረፍ የድርጅቱን ማኅበረሰብ በማሳተፍ አቅምን ማጎልበትና የቤተክርስቲያኒቱን ተጨባጭ አሁናዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የገንዘብ አስተዳደሩን እና የመረጀ መለዋወጫ መስመሩን ደረጃውን የጠበቀ የቴክኖሎጂ ልማት በማበልጸግ የቤተክርስቲያኒቱ ይዞታዎች ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉ ማድረግና ደንበኞች በባለቤትነት ስሜት እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ ነው፡፡
የድርጅቱ ዕሴቶች
- ውጤታማነት፦ የተፋጠነ ልማት፣መልካም አስተዳደር፣የተሸለ ሥርዓት መዘርጋት፣ የመረጃ ልውውጥ መንገዱን ማዘመንና ውጤታማነትን ሊያረጋግጥ የሚችል አቅም መፍጠር፡፡
- ቅልጥፍና፦ ደንበኛ ተኮር ሥርዓትን ዘርግቶ ደንበኛን ማመላለስ እንዳይፈጠር አቅም በፈቀደ መልኩ የሥራ ክፍፍል አድርጎ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት መቻል ፡፡
- በጥናት ላይ የተመሠረት ምላሽ መስጠት፦ የቤቶች ችግሮች ፣ የደንበኛ አያያዝ ችግሮች፣ እና መሰል ችግሮችን ግልጸኝነት፣ ተጠያቂነት ፍትሐዊነት እና ከአድልዎ በጸዳ መልኩ መፍታት፡፡
የድርጅቱ ዓላማ
- የቤት ልማት ዘርፉን በማዘመን ምቹ፣ጽዱ፣ውብ፣ ማራኪና ለነዋሪዎች ተስማሚ የሆኑ ቤቶችን ማልማትና ተመራጭነትን ማደበር
- ቤተክርስቲያኒቱ በተሰማራችበት የቤቶች ልማት በሀገር ውስጥ ካሉ ተመሳሳይ ተቋማት ጋር ጥሩ ተፎካካሪ በመሆን የተሻለ ገቢ በመፍጠር የቤተክርስቲያንን ውስጣዊ ኢኮኖሚ እንዲጠናከር በማድረግ መንፈሳዊ ተልኮዋን በብቃት እንድትወጣ ማስቻል፡፡
- የድርጅቱን ገቢ ማሳደግ፣ውጤታማነትና ትርፋማነትን ለማሻሻል ጥረት ማድረግ ነው፡፡
- ከቤተክርቲያኒቱ የኢኮኖሚ አቅም ጋር የተገናዘበና የማያቋርጥ የልማት ስትራቴጂ መንደፍ፣
- የድርጅቱን ውሳኔ አሰጣጥ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ተጠያቂነት ላይ ያተኮረ ድጋፍ የሚሰጥ አስተዳደር መዘርጋትና በሥራ ላይ ማዋል፡፡
