አገልግሎቶች
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት ዋና ዋና አገልግሎቶች
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን የሚሠራ ሲሆን በዋናነት ከሚያከናውናቸው አገልግሎቶቹ መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡
1. የቤት ልማት መርሐ-ግብር
ስለ ቤቶችና ሕንጻዎች ልማትና አስተዳደር ድርጅት ጥናት በማካሄድ የልማት ፕሮጀከት በመንደፍ፣ የአሠራር መመሪያ በማበልጸግና ሲፈቀድ ተግባራዊ የማድረግ አገለግሎት የሚሰጥ ሲሆን የአዳዲስ ቤቶችንና ሕንጻዎችን ግንባታ ዋናው መሥሪያ ቤት ሲፈቀድ ማሠራት ማልማትና ከቤተ ክርስቲያኗ በሚሰጠው ውሳኔና ፈቃድ ብቻ ቤቶችና ሕንጻዎችን የመግዛት ከባንክ የመበደር ፖሊሲ ነክ በሆኑ ጉዳዮች ላደ ከሦስተኛ ወገን ጋር ግንኙነት የማድረግ እንዲሁም ሌሎች ከቤቶችና ሕንጻዎች ጋር የተያያዙ ተዛማጅ ሥራዎችን የማከናወን አገልግሎት ይሰጣል፡፡
2. የደንበኞች አገለግሎት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የደንበኞች አገልግሎት በሚባል የድርጅቱ ዋና ክፍል የሚመራ ደንበኞችን መሠረት ያደረገ ሥራ የሚሠራ ሲሆን የቤት ኪራይ ተመን ጥናት በማካሄድና ሲፈቀድ ተግባራዊ ከማድረግ ጀምሮ የመኖሪያ ቤት ኪራይ፣ የንግድ ቤት ኪራይ፣የውል እድሳት ሥራ ፣ የስም ዝውውር ሥራ፣ የዘርፍ ለውጥ ሥራ እና መሰል ከደንበኞች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሥራ ይሠራል፡፡
3. የጥገናና የእድሳት አገለግሎት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የሚያስተዳድራቸው ቤቶችና ሕንጻዎች በመመሪያው መሠረት ተገቢውን እንከብካቤ፤ ጥገናና ዕድሳት የማድረግ አገለግሎት ይሰጣል፡፡
4. የድርጅቱ የኪራይ ገቢዎችን በአግባቡ መሰበስብ
ድርጅቱ የሚያስተዳድራቸውን የቤቶችና ሕንጻዎችን በመመሪያ መሠረት ኪራያቸውን የመተመን፣ የማከራየት ፣ የኪራይ ሂሳብ በወቅቱ የመሰብሰብና ገቢ የማድረግ አገልግሎት ይሰጣል፡፡
